Tuesday, August 4, 2009

በኢጣሊያ የወረራ ዘመን (1928ዓ.ም)የተፈጸመ የመነኮሳትና ካህነናት ጭፈፍጨፋ

        

            ፋሺስት  ኢጣልያ 1928 ዓ.ም  ኢትዮጵያን  በወረረበት  ጊዜ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክረስቲያኖች፣ ካህናት፣መነኮሳት  ላይ   ያደረሰዉ   ጭ ፍጨ ፋ  እጅግ ዘግናኝ  ነበር፡፡በመነኮሳት  ላይ  እና  በካህናት  ላይ  ያደረሰዉን  ዘግናኝ የጅምላ

ጭ ፍጨ ፋ  ስንመ ለከት-

1.      በሐምሌ  22  ቀን 1929 ዓ.ም   አቡነጴጥሮስ  በአ.አ  ከተማ ፡፡

2.      በኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ. ም  አቡነ ሚካኤል  በጎሬ ላይ ታረዱ፡፡

3.      በግንቦት 13 ቀን 1929 ዓ.ም የደብረ ሊባኖስ ገዳም  መነኮሳት በጸሎት ላይ እንዳሉ 682 መነኮሳት  ተገድለዋል፡፡

4.      ግንቦት 23 ቀን 1929 ዓ.ም የዜና ማርቆስ ካህናት  በቅዳሴ ላይ እንዳሉ  በመምህር ወልደ ሚካኤል ቀዳሽነት  43  መነኮሳት  ተገድለዋል፡፡

5.       በሰኔ 12 ቀን 1929 ዓ.ም የዝቋላ ገዳም  መነኮሳት  በማስታኮት ላይ እንዳሉ 211 መነኮሳት ታረዱ በዚህ ጊዜ ደመና መጥቶ ሸፈናቸው  በዜና ማርቆስም ደመናው  ጋረዳቸዉ፡፡

6.      በሰኔ 3 ቀን 1929 ዓ. ም   የምድረ  ከብድ  ገዳም 60 መነኮሳት  ታረዱ፡፡

7.      በሰኔ 15 ቀን 1929 ዓ.ም የአሰቦት   ደብረ  ወገግ  መነኮሳት 91 ታረዱ ፡፡

8.      በኅዳር 25 ቀን 1929 ዓ.ም የአዲስ ዓለም ካህናት በአሰቃቂ ሁኔታ ታረዱ  ብዛታቸዉ 135 ነበር፡፡

9.      ጥቅምት 17 ቀን 1929 ዓ.ም   የደብረ ዳሞ  ገዳም 416 መነኮሳት በታረዱበት ጊዜ ልዪ ታምራት ታየ ብርሃን ወርዶ  ታየ፡፡

10.  መጋቢት 16 ቀን 1929 ዓ.ም   የማ     ኅበረ  ሥ ላሴ ገዳም መነኮሳት ጠባቂዎች ሳይቀሩ 513 ተገደሉ  በዚህም  ቀን  የደብረ አባይ  ገዳም  ተመዘበረ፡፡

11.  በሚ ያዝያ 18 ቀን 1929 ዓ.ም  እና ሚያዝያ 20 ቀን 1929 ዓ.ም  የመርጡ ለ ማርያምና የተድባበ  ማርያም  ካህናት 363  በጭ ካኔ  ታረዱ፡፡

12.   በሐምሌ 29 ቀን 1929 ዓ.ም የጎንደር ሊቃዉንት ተለቅመዉ ከታሰሩ በኅላ ግማሾቹ ተገደሉ የ ቀሩት በስር  ቤት  ተሰቃዩ ፡፡

13.  ታኀሳስ 7 ቀን 1928 ዓ.ም  አርብ  በ9 ሰዓት  ብሉይ  ክፍሌ  በግፍ  ተገደሉ፡፡

14.  የካቲት 18 ቀን 1929 ዓ.ም የየካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ 11 ሊቃዉንት  ተጠርተዉ   ስቃይ ወደአለበት ቦታ ተወስደዉ  ታሠሩና ግማሾቹ  ተገደሉ፡፡

              ይህ በታላላቅ ደብራትና ገዳማት ላይ የተፈጸሙ   እና ተመዝግበዉ የሚታወቁ ሲሆኑ  ሳይመዘገቡ  የቀሩ ብዙ እዳሉ  የሚ ገመ ት ሲሆን የሞቱት  ቁጥር ከዚህም  ይበልጣል፡፡

                              የአባቶቻችን ረድኤትና በረከታቸዉ  አይለየን፤

 


Wednesday, July 29, 2009

Sunday, May 24, 2009


ኢትዮጵያ በኢጣልያ ፋሽስቶች የወረራ አመታት 1928-1933 ዓ ም

ደራሲ- አልቢርቶ ሰባኪ