ፋሺስት ኢጣልያ 1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክረስቲያኖች፣ ካህናት፣መነኮሳት ላይ ያደረሰዉ ጭ ፍጨ ፋ እጅግ ዘግናኝ ነበር፡፡በመነኮሳት ላይ እና በካህናት ላይ ያደረሰዉን ዘግናኝ የጅምላ ጭ ፍጨ ፋ ስንመ ለከት- 1. በሐምሌ 22 ቀን 1929 ዓ.ም አቡነጴጥሮስ በአ.አ ከተማ ፡፡ 2. በኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ. ም አቡነ ሚካኤል በጎሬ ላይ ታረዱ፡፡ 3. በግንቦት 13 ቀን 1929 ዓ.ም የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኮሳት በጸሎት ላይ እንዳሉ 682 መነኮሳት ተገድለዋል፡፡ 4. ግንቦት 23 ቀን 1929 ዓ.ም የዜና ማርቆስ ካህናት በቅዳሴ ላይ እንዳሉ በመምህር ወልደ ሚካኤል ቀዳሽነት 43 መነኮሳት ተገድለዋል፡፡ 5. በሰኔ 12 ቀን 1929 ዓ.ም የዝቋላ ገዳም መነኮሳት በማስታኮት ላይ እንዳሉ 211 መነኮሳት ታረዱ በዚህ ጊዜ ደመና መጥቶ ሸፈናቸው በዜና ማርቆስም ደመናው ጋረዳቸዉ፡፡ 6. በሰኔ 3 ቀን 1929 ዓ. ም የምድረ ከብድ ገዳም 60 መነኮሳት ታረዱ፡፡ 7. በሰኔ 15 ቀን 1929 ዓ.ም የአሰቦት ደብረ ወገግ መነኮሳት 91 ታረዱ ፡፡ 8. በኅዳር 25 ቀን 1929 ዓ.ም የአዲስ ዓለም ካህናት በአሰቃቂ ሁኔታ ታረዱ ብዛታቸዉ 135 ነበር፡፡ 9. ጥቅምት 17 ቀን 1929 ዓ.ም የደብረ ዳሞ ገዳም 416 መነኮሳት በታረዱበት ጊዜ ልዪ ታምራት ታየ ብርሃን ወርዶ ታየ፡፡ 10. መጋቢት 16 ቀን 1929 ዓ.ም የማ ኅበረ ሥ ላሴ ገዳም መነኮሳት ጠባቂዎች ሳይቀሩ 513 ተገደሉ በዚህም ቀን የደብረ አባይ ገዳም ተመዘበረ፡፡ 11. በሚ ያዝያ 18 ቀን 1929 ዓ.ም እና ሚያዝያ 20 ቀን 1929 ዓ.ም የመርጡ ለ ማርያምና የተድባበ ማርያም ካህናት 363 በጭ ካኔ ታረዱ፡፡ 12. በሐምሌ 29 ቀን 1929 ዓ.ም የጎንደር ሊቃዉንት ተለቅመዉ ከታሰሩ በኅላ ግማሾቹ ተገደሉ የ ቀሩት በስር ቤት ተሰቃዩ ፡፡ 13. ታኀሳስ 7 ቀን 1928 ዓ.ም አርብ በ9 ሰዓት ብሉይ ክፍሌ በግፍ ተገደሉ፡፡ 14. የካቲት 18 ቀን 1929 ዓ.ም የየካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ 11 ሊቃዉንት ተጠርተዉ ስቃይ ወደአለበት ቦታ ተወስደዉ ታሠሩና ግማሾቹ ተገደሉ፡፡ ይህ በታላላቅ ደብራትና ገዳማት ላይ የተፈጸሙ እና ተመዝግበዉ የሚታወቁ ሲሆኑ ሳይመዘገቡ የቀሩ ብዙ እዳሉ የሚ ገመ ት ሲሆን የሞቱት ቁጥር ከዚህም ይበልጣል፡፡ የአባቶቻችን ረድኤትና በረከታቸዉ አይለየን፤ |
Tuesday, August 4, 2009
በኢጣሊያ የወረራ ዘመን (1928ዓ.ም)የተፈጸመ የመነኮሳትና ካህነናት ጭፈፍጨፋ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment